ኢየሱስ ይወዳችኋል

በዓለም ላይ የማንረዳቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡ከነዚህ መካከልም ጦርነት፣ ረሐብ፣ በግል የሚያጋጥሙን ችግሮች እና ሞት ይጠቀሳሉ፡፡

እግዚአብሔር ፍቅር ከሆነ፣ እነዚህ ሁሉ ነገሮች እንዲሆኑ ለምን ይፈቅዳል?” ብለን እንጠይቅም ይሆናል፡፡ በእርግጥ የእነዚህ ነገሮች ሁሉ መልስ እኛም የለንም፡፡ አዎ፣ የጥያቄዎች ሁሉ መልስ የለንም፤ ነገር ግን አንድ ነገር ደግሞ እናውቃለን፡

ያም ኢየሱስ እኛን መውደዱ ነው!

መውደዱን ግን እንዴት እናውቃለን? ኢየሱስ ራሱ አንድ ጊዜ እንደተናገረው “ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም።“

ኢየሱስ ያደረገው ይህን ነው፡

ስለሰው ልጆች ራሱን ሰጥቷል፡፡ ያንን ማድረግ ግን ነበረበት?

ውቃለህ፣ መሆን ነበረበት። በዓለም ያለው ክፋት ሁሉ መነሻው እኛ የሰው ልጆች ኃጢአት መሥራታችን ነው፡፡

ኃጢአት ሰዎችን ከሰዎች እንዲሁም ሰዎችን ከእግዚአብሔር ይለያል፡፡

ኃጢአት ሰላምን ያጠፋል፡፡

ኃጢአት ቅጣትን ያስከትላል፡፡

ኢየሱስ የእኛን ኃጢአት በራሱ ተሸከመ፡፡ የእኛን ሰላም ለመመለስ የእኛን ቅጣት እርሱ እንደ ተቀበለ ነቢዩ ኢሳይያስ የነገረን ገና ድሮ ነው፡፡

ያንን ያደረገውም ጌታችን ኢየሱስ በእጅጉ ስለሚወደን ነው፤ በሃሳቡ ውስጥ ያለነው ገና ሳንወለድ ጀምሮም ነው፡፡

ኢየሱስ የሞተልን እኛ እንድንኖር ከእግዚአብሔርና ከሰዎች ጋር ኅብረት ሆነን ለዘላለም እንድንኖር ነው።

እና ኢየሱስ ዛሬም ይወደናል!

እርሱ ቢሞትም አሁን ግን ሕያው ነው፤ ምክንያቱም አብ አባቱ ከሙታን አስነስቶታል፡፡

ኢየሱስ እንደ እኛ ሰው ሆኖ ወደዚህ ምድር ስለመጣ፣ እኛ የምናልፍባቸውን አስቸጋሪ እና አስጨናቂ ሁኔታዎች ሁሉ ያውቃቸዋል፡፡

እሱ የእርስዎን ጥያቄዎች እና ችግሮች ይረዳል. ይሁን እንጂ ማንንም ሰው ፍቅሩን እንዲቀበል አያስገድድም. አንተም የእሱን ፍቅር ለመቀበል እድሉ አለህ።

ፍቅሩን ተቀብለን አወቅን፡ እውነት ነው!

ኢየሱስ በህይወታችን የእረፍት፣ የሰላም እና የደስታ ምንጭ ሆኗል። ስንጸልይ ኢየሱስ ይሰማናል። በአስቸጋሪ ጊዜ እና ሁኔታ ውስጥም እንኳን ቢሆን፣ መጽናናት እና ብርታትን ይሰጠናል፡፡

ስለኢየሱስ የበለጠ ማወቅ ትፈልጉ ይሆን? የምትፈልጉ ከሆነ ፍላጎታችሁን በጸሎት ለእርሱ ንገሩት፤ ስለእርሱ ፍቅር፣ ሰላም፣ እረፍት እና ደስታ የተረዱ አማኞች በአካባቢያችሁ ካሉም፣ እነርሱን አናግሯቸው፡፡ ወይም ይፃፉልን።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይባርካችሁ!

Die Kommentare sind geschlossen.